Fana: At a Speed of Life!

የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በባሕር ዳር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የመተከልና አካባቢው ኮማንድ ፖስት አፈጻጸምን በተመለከተ በባሕር ዳር ተወያይተዋል።

አፈጻጸሙ የተገመገመው የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ተመሥገን ጥሩነህና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን በተገኙበት ነው።

ውይይቱ የሁለቱ ክልሎች ተቀራርቦ የመሥራት ውጤትም ቀጠናው ከዚህ በላይ ሰላማዊ እና የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበት እንዲሆን እንደሚያስችለው ታምኖበታል።

በሁለቱ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎች በነበረው አለመረጋጋት ከ49 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው እንደነበር የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን መግለጹ ይታወሳል።

ባለፉት ወራት በቀጠናው አንጻራዊ ሰላም መፈጠሩን ተከትሎ ደግሞ ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንደተመለሱ መገለፁን አብመድ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.