Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ሕገ ወጥ መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ለ45 ቀናት ክትትል ሲደረግባቸው የቆዩ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ በማዘዋወር የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡
መነሻቸውን ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አርጡ ፉርሲ ወረዳ ጪረቲ ቀበሌ አድርገው እስከ ሰሜን ወሎ ወልዲያ ድረስ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ ነቀሩ የተባሉ ግለሰቦች በተደረገ ዘመቻ በቁጥጥር ስር ውለው እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል።
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል የበላይ ክፍለ ጦር 5ኛ ሬጅመንት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ምትኩ ሞላ እንደገለፁት÷ በተካሄደው ዘመቻ የተያዙት መሳሪያዎች ተጠርጣሪዎቹ ለአሸባሪው ህወሓት እና ተላላኪው ሸኔ ሊተላለፍ የነበረ ነው፡፡
ይህን ሕገ ወጥ ተግባር ከቦታ ቦታ የሚያዘዋውሩት በቤት መኪና፣ አንቡላንስና ሌሎች ተሸከርካሪዎችን በመጠቀም መሆኑን ገልጸዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
በተደረገው ዘመቻም 2 ዲሽቃ፣ 1 ብሬን፣ 1 ባለ አንድ እግር ታጣፊ ክላሽ እንኮቭ፣ 1 እስታር ሽጉጥ ፣ 340 የክላሽ እንኮቭ ጥይት፣ 5 የብሬን ጥይት፣12 የሽጉጥ ጥይት፣ 4 የክላሽ መጋዘን፣ 1 የሽጉጥ መጋዘን ፣ አንድ “ሱዙኪ” የቤት መኪና እና 185 ሺህ ብር ተይዟል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.