Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ባህርዳርን ጨምሮ በ4 ከተሞች ማንኛውም አይነት የህዝብና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ኮሮና የቫይረስ መከላከል እና መቆጣጠር ኮማንድ ፖስት ባህርዳርን ጨምሮ በአራት ከተሞች ማንኛውም አይነት የህዝብ እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ውሳኔ አሳለፈ።

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ይርሳው በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ፥ ማንኛውም አይነት የህዝብ እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳይኖር የተከለከለባቸው ከተሞችም ባህርዳር፣ አዲስ ቅዳም፣ ቲሊሊ እና እንጅባራ ናቸው።

በከተሞቹ ከነገ 6 : 00 ስዓት ጀምሮ ለ14 ቀን የሚቆይ ማንኛውም አይነት የህዝብ እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ተወስኗል።

አቶ ጌትነት ይርሳው አክለውም፥ በአራቱ ከተሞች ቫይረሱን ለመከላከል የሚግዙ ግባአቶች ግን በልዩ ትኩረት ተሰጥቶአቸው 24 ስአት እንደሚሰራ ይደረጋል ብለዋል።

እገዳው በልዩ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ የደረቅና የፈሳሽ ጭነት ተችከርካሪዎችን እንዲሁም የውኃና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች አይጨምርም ያሉት አቶ ጌትነት፥ የድንገተኛ አገልግሎት የሚሰጡና የወረርሽኙ በጎ ፍቃደኞች ግን መንቀሳቀስ እንደሚችሉም አስታውቀዋል።

መመሪዎችን ተላልፈው የሚገኙ ሰዎችን በህግ ተጠያቂ የሚደረጉ መሆኑን በመግለጽ፤ የፀጥታ አካላት ኃላፊነት እንደወሰደም ገልፀዋል።

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.