Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከ88 ሚሊየን ብር በላይ ሊሰወር የነበረ ግብር መሰብሰቡን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ባለፈው አመት ከ88 ሚሊየን ብር በላይ ሊሰወር የነበረ ግብር መሰብሰብ መቻሉን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ባለፈው ዓመት የግብር ከፋዮችን ህግ ተገዥነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች መስራቱን፥ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ብዙአየሁ ቢያዝን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከ5 ሺህ 344 ግብር ከፋዮች የተሰወረ ከ88 ሚሊየን 588 ሺህ በላይ ብር መሰብሰብ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

ሃላፊዋ በ2013 ዓ.ም 20 ነጥብ 56 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱንም ነው የተናገሩት፡፡

በተመሳሳይም በሃሰተኛ ደረሰኝ ሊሰራ የነበረ ከ368 ሚሊየን በላይ ብር መዳን መቻሉም ተገልጿል፡፡

በዚህ ዓመት የግብር ከፋዮችን ህግ ተገዥነት ለማሣደግ የንቅናቄ ስራ ከጥቅምት15 እስከ ህዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም ይካሄዳልም ተብሏል፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.