Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ 8 ተሽከርካሪዎችን በድጋፍ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስ ኤይድ) ለአማራ ክልል ጤና ቢሮ ስምንት ተሸከርካሪዎችን አበረከተ፡፡
የዩኤስ ኤይድ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሽን ጆንስ በርክክቡ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ በክልሉ በነበረው ጦርነት ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ መቋቋም ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም ለጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውሉ ስምንት ተሽከርካሪዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸው÷ የማህበረሰቡን ጤና ለማሻሻል አስተዋጽዖ ይኖራቸዋል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መልካሙ አብቴ÷ ክልሉ ባጋጠመው ጦርነት የወደሙና የተዘረፉ ጤና ተቋማትን መልሶ በማደራጀት ሥራ ለማስጀመር ድርጅቱ የህክምና መሣሪያና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰው ማመስገናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
በጦርነቱ ያጋጠሙ ችግሮች ሰፊ መሆናቸውን ገልጸው፥ ድጋፍና ዕገዛቸው እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.