Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ኢራንና እና ሩሲያ የመራጮች መረጃ እንዳላቸው አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ የጸጥታ ኃላፊዎች ኢራንና እና ሩሲያ የመራጮች መረጃ አላቸው ሲሉ ገለጹ፡፡

የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ ኢራን ለዴሞክራት መራጮች ዛቻ ያዘሉ የኢሜል መልዕክቶችን ልከዋል በሚል ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

በተለይም ኢራን ወደ መራጮች ልካቸዋለች የተባሉት የኢሜል መልዕክቶች በቀኝ ዘመሞቹ የትራምፕ ደጋፊዎች የተላኩ በማስመሰል በአሜሪካ ቀውስ ለመፍጠር ያለሙ ናቸው ብለዋል፡፡

አሁን ይፋ የተደረገው መግለጫ ምርጫ በተቃረበበት ወቅት ያልተለመደ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የሀገሪቱ መንግስት መራጮች ከውጭ ኃይሎች በሚሰነዘሩ የሐሰተኛ መረጃዎች ስርጭት አማካኝነት እንዳይጠለፉ ስጋት እንደገባው ማሳያም ነው ተብሏል፡፡

በአሜሪካ አብዛኛዎቹ ግዛቶች ውስጥ የመራጮች መረጃ በይፋ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ሃገራቱ እንዴት እንዳገኙት ግን ኃላፊዎቹ ያሉት ነገር የለም፡፡

የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ዳይሬክተር ክርስቶፈር ሬይ የአሜሪካ የምርጫ ስርዓት አሁንም ቢሆን አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

መራጮችም ድምጻቸው እንደሚቆጠር እርግጠኛ መሆን አለባቸውም ነው ያሉት፡፡

በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና በዴሞክራቱ እጩ ጆ ባይደን መካከል የሚደረገው የ2020 የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ 11 ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.