የአሜሪካ የበጀት ጉድለት ወደ 3 ትሪሊየን ዶላር ከፍ አለ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የዩናይትድ ስቴትስ የበጀት ጉድለት ወደ 3 ትሪሊየን ዶላር ከፍ ማለቱ ተነገረ።
የበጀት ጉድለቱን የሀገሪቱ የፌደራል መንግስት ለኮሮናቫይረስ ማገገሚያ ያዋለው ገንዘብ እንዳናረው ነው የተመለከተው”
የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ባለፉት 11 ወራት የፌደራል መንግስቱ 6 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ያደረገ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 2 ትሪሊየን ዶላሩ ለኮሮናቫይረስ የኢኮኖሚ ጫና መከላከያ የዋለ ነው ።
እንደ ሪፖርቱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመከሰቱም በፊት የሀገሪቱ የበጀት ጉድለት ወደ 1 ትሪሊየን ዶላር ወደ መሆን እየተጠጋ ነበር ነው የተባለው።
በበጀት ዓመታቸው ማብቂያ ላይ የፌደራል መንግስቱ የበጀት ጉድለት 3 ነጥብ 3 ትሪሊየን ዶላር ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ይህም መጠን ከአምናው በሶስት እጥፍ የበለጠ ነው።
የሀገሪቱም አጠቃላይ እዳ 26 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር ይበልጣል ተብሎ ይጠበቃል ።
ምንጭ፦ ቢቢሲ