Fana: At a Speed of Life!

 የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ለመምከር ሱዳን እና ግብፅን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ ስቴቨን ሙንሽን የህዳሴ ግድብን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ለመምከር ሱዳን እና ግብፅን እየጎበኙ ይገኛሉ።

በትናንትናው ዕለትም ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ጋር የታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሚኒስትሩ ከህዳሴ ግድብ ጋር ተይይዞ ሀገራቱ ያሏቸውን ልዩነቶች በፍትሃዊነት እንዲፈቱ ማሳሰባቸውን በካይሮ የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ እና የግምጃ ቤት ሃላፊው በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ነው የተነገረው።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ ስቴቨን ሙንሽን በሱዳን በዛሬው ዕለት ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን በተመሳሳይ በተለያዩ ጉዳዮች ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ ስቴቨን ሙንሽን  በኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል በአሜሪካ ታዛቢነት የተካሄደውን እና ኢትዮጵያ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነትን የተቃወመችበትን ውይይት ሲመሩ የነበሩ መሆናቸው የሚታወስ ነው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.