Fana: At a Speed of Life!

የአምባሳደር ስዩም መስፍን ባለቤትና ወንድ ልጁ ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር የዋሉት የአምባሳደር ስዩም መስፍን የትዳር አጋር ወይዘሮ ፈለገህይወት በርሔና ልጃቸው አጋዚ ስዩም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ከመስከረም 30 በኋላ መንግስት የለም በማለት ከህወሓት ፀረ ሰላም ቡድኖችና ከኦነግ ሸኔ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል በአዲስ አበባ ሁከትና አመፅ ለመቀስቀስ ገንዘብ በማሰራጨትና ወጣቶችን በመመልመል ተጠርጥረው መያዛቸውን መርማሪ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በስዩም መስፍን ስም በተመዘገበ የመንግስት ቤቶች እና በፀሀይ ሪል እስቴት ውስጥ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ላይ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ምርመራ ተደርጓል ሲል መርማሪ ፖሊስ አስረድቷል፡፡

በተለይም በመንግስት ቤቶች በተደረገው ፍተሻ ሁለት ሽጉጦች ተገኝተዋል፡፡

እንዲሁም በፀሀይ ሪል እስቴት በሚገኝ መኖሪያ በተደረገ ብርበራ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ማግኘቱን መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል ሲልም አስረድቷል፡፡

የአቶ ስዩም መስፍን ባለቤት ወይዘሮ ፈለገህይወት አንደኛው ሽጉጥ ባላቤቴ ራሱን የሚጠብቅበት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከውጭ ሀገር በስጦታ የተሰጠው ነው ስትል አብራርታለች፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ዋስትና እንዲሰጣቸው የጠየቁም ሲሆን፤ ወይዘሮዋ ልጄ አጋዚ የአዕምሮ ህመምተኛ ስለሆነ መድሃኒት እንዲገባልን ስትል ጠይቃለች፡፡

ጉዳዩን የተከታተለው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለተጨማሪ ምርመራ 8 ተጨማሪ ቀናት በመፍቀድ፣ ለፖሊስ በታሰሩበት ቦታ አስፈላጊው መድሀኒት እንዲገባላቸው አዟል፡፡

ታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.