Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሀይማኖት አባቶች ጋር በመሆን መርሃግብሩን በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ቅጥር ግቢ በይፋ አስጀምረዋል።

የሀይማኖት አባቶቹ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በችግኝ ተከላው እንዲሳተፍና ተፈጥሮን እንዲጠብቅ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የተተከሉትን መንከባከብም መዘንጋት እንደሌለበት አሳስበዋል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የሚተከሉት ችግኞች አካባቢን አረንጓዴ ከማድረግና ስነምህዳሩን ከማስተካከል አልፈው ምግብም መሆን የሚችሉ ናቸው ብለዋል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ 5 ቢሊየን ችግኝ የሚተከል ሲሆን በአዲስ አበባ ደረጃ ደግሞ 7 ሚሊየን ችግኝ የሚተከል ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.