Fana: At a Speed of Life!

የአራተኛ ትውልድ ኤል ቲ ኢ አገልግሎት በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የአራተኛ ትውልድ (4ጂ) ኤል ቲ ኢ አገልግሎትን በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን በይፋ አስጀመረ።

አገልግሎቱ በደቡብ ክልል ስድስት ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን በወላይታ ሶዶ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።
አገልግሎቱ በወላይታ ሶዶ፣ ወልቂጤ፣ ጂንካ፣ አርባምንጭ፣ ቡታጅራ እና ሆሳዕና ከተሞች 600 ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ አገልግሎቱን በሃገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የማስፋፋት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

የቴሌኮም ማስፋፊያ ስራ የተቋሙን ገቢ ከማሳደግ ባለፈ ከተሞች እንዲለሙ፣ የስራ እድል እንዲፈጠር፣ የስራ አማራጮችን ለማስፋት፣ ምርታና ምርታማነትን ለማሳደግ ብሎም ሻጭና ገዢን በቀላሉ ለማገናኘት እንዲሁም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴን ለማቃለል ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

ለረጅም አመት በአዲስ አበባ ብቻ የነበረውን አገልግሎት ወደ ተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች በማስፋፋት የኢኮኖሚ እድገቱን በማሳደግ ዜጎች በአካባቢያቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ሚናው ከፍ ያለ መሆኑንም ገልጸዋል።

የአራተኛ ትውልድ ኤል ቲ ኢ አገልግሎትን የማስፋት ስራ በ103 ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በሃይማኖት ኢያሱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.