Fana: At a Speed of Life!

የአርባምንጩ ግብ ጠባቂ ፍሬው ገረመው ህይወቱ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ግብ ጠባቂ ፍሬው ገረመው ህይወቱ አለፈ።

ፍሬው ገረመው በድንገት ህይወቱ እንዳለፈ እና እስከ ትናትናው ዕለት ልምምድ ሲሰራ መቆየቱ ነው የተነገረው።

ግብ ጠባቂው ከሰሞኑ በጉልበቱ ላይ እጢ ወጥቶበት የነበረ ሲሆን በትናትናው ዕለት ልምምድ ከሰራ በኋላ በጉልበቱ ላይ የወጣውን እጢ ለማስወጣት ወደ ህክምና ተቋም አምርቶ በዛሬው ዕለት ህይወቱ ማለፉን ሶኮር ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ለጂንካ ከተማ ፣ ለሻሸመኔ ከተማ እና ለደቡብ ፓሊስ እግር ኳስ ክለቦች ተጫውቷል።

በክረምቱ የዝውውር መስኮት በፕሪምየር ሊግ እና በከፍተኛ ሊግ ክለቦች ሲፈለግ የነበረው ፍሬው ተወልዶ ያደገበትን አርባምንጭ ከተማ ምርጫው በማድረግ ለክለቡ ውጤታማነት ከፍተኛ ሚና ነበረው ተብሏል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.