Fana: At a Speed of Life!

የአርብቶ አደር አካባቢ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ የሚውል 200 የሞተር ሳይክል ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 11 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች የአርብቶአደሩን ማህበረሰብ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ልዩ ልዩ የልማትፕሮጀክቶች ተቀርፀው እየተሠሩ መሆኑን በሰላም ሚኒስቴር የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ አስታወቀ።

ማስተባባሪያው የመንገድ መሠረተ-ልማት ተደራሽ ባልሆኑባቸው ቆላማ የአርብቶአደር አካባቢዎች የሚሠሩ ፕሮጀክቶችን እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን አፈጻፀም ለማቀለጠፍ የሚረዳ 200 የሞተር ሳይክል ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፉ ለሶማሌ 72፣ ለአፋር 40፣ ለኦሮሚያ 36፣ ለደቡብ 18  ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ 18 እንዲሁም ለጋምቤለ 16 ሞተር ሳይክሎችን ያሰራጨ ሲሆን ከስድስቱም ክልሎች የሚመለከታቸው ተወካዮች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።

የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመጥቀስም በቅርብ ቀን የ81 መኪናዎች ድጋፍ እንደሚደረግ የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን መግለጻቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.