Fana: At a Speed of Life!

ዓለም የደረሰበትን የኢንዱስትሪ አብዮት ተመልካች እና ተቀባይ ብቻ የሚሆን ወጣት እንዲኖረን አንሻም- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን ዛሬ መርቀው ከፍተዋል።
ይህን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰው ልጅን መስተጋብር በተለያዩ ነባራዊ ጥናቶች ላይ በማንተራስ ፤ ልዩ የቴክኖሎጂ ልምምዶችን በመጠቀም ኮምፒውተራይዝድ ማሽኖችን ለእውናዊ መፍትሔ የማሣለጥ ዐቅም መሆኑን በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
እንዲሁም ዓለም የደረሰበትን የኢንዱስትሪ አብዮት ተመልካች እና ተቀባይ ብቻ የሚሆን ወጣት እንዲኖረን አንሻም ነው ያሉት።
ጀማሪ የሥራ ዕድል ፈጣሪዎችን በቴክኖሎጂ ዐቅም ግንባታ እና በምርምር ልህቀት ላይ በማገዝ ፤ ተግባራዊ እና ችግር ፈቺ የሆኑ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች የሚበለጽጉበት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን መርቀው በመክፈታቸው የተሰማቸውን ደስታም ገልፀዋል።
እንዲሁም ቴክኖሎጂን መጠቀምን ጨምሮ፣ የማክሮ ኢኮኖሚያችንን ከባቢ ለማመጣጠን ወሳኝ ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ ወቅት፣ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን የሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተባባሪዎች ሆናችሁ እንዳትገኙ ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ዛሬ የተመረቀው ማዕከሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሃሳብ አመንጪነት የተገነባ መሆኑም ታውቋል፡፡
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የተለያዩ ዘርፎችን ለማዘመን ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል የተባለ ሲሆን ÷በተለይ በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የበኩሉን ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ዘርፉ በጤና፣በትራንስፖርት፣በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ሌሎች ዘርፎችም አስተዋፆ ይኖረዋል ነው የተባለው።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በሰው ጉልበት የሚከናወኑ ተግባራርን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የገንዝብ፣ የጊዜ እና ጉልበት ብክነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማስቀረት ያስችላል።
የማዕከሉ መከፈትም በኢትዮጵያ ያለውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ጅማሬ ወደተሻለ ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በምርቃት ስነ- ስርዓቱ ላይ ዘርፉን የተመለከተ አውደ ርዕይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተጎብኝቷል።
በምስክር ስናፍቅ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.