Fana: At a Speed of Life!

የአሰላ ከተማ ፖሊስ በፀጥታ እና ሰላም ማስከበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሰላ ከተማ ፖሊስ በፀጥታ እና ሰላም ማስከበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት እውቅና ሰጠ።
 
የከተማዋ ፖሊስ በስነ ምግባር እና በስራቸው መልካም አፈፃፀም ላሳዩ የፖሊስ አባላት ነው እውቅና የሰጠው።
 
በዚህ መሰረትም ከወታደር እስከ ዋና ሳጅን ድረስ ለ84 የፖሊስ አባላት ማዕረጉ ተሰጥቷል።
 
የከተማው ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ጋዲሳ ሁንዴ÷ በ2013 ዓ.ም በምርጫ እና በአጠቃላይ በፀጥታ ዘርፍ ለተሰራው ስራና ለተገኘው ውጤት በጎ አስተዋጽኦ የነበራቸው የፀጥታ እና የህብረተሰቡን ክፍሎችን አመስግነዋል።
 
የነበሩ መልካም አፈፃፀሞችን በማስቀጠል በቀጣይ እቅዶችና ሀገራዊ ተግባራት ላይ ለመሳተፍ ቁርጠኝነት እንዳለም ተናግረዋል።
 
በመድረኩ ለፀጥታ አካላት፣ በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ለተሳተፉ አካላት፣ ለአባገዳዎች፣ ለሃይማኖት አባቶች እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋና እና እውቅና ተሰጥቷል።
 
በቅድስት ዘውዱ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.