Fana: At a Speed of Life!

የአስተዳደሩ የሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት በአዲስ መልክ ተደራጀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ዛሬ በአዲስ መልክ ተደራጀ።

ምክር ቤቱ በአዲስ መልክ የተደራጀው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች በግድቡ ግንባታ የተፈጠረውን ብሔራዊ መግባባትና መነሳሳት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መሆኑም በስብሰባው ላይ ተገልጿል።

ምክር ቤቱ ሕዝቡ ለግድቡ ግንባታ የሚያደርገውን ተሳትፎ በማጠናከር የሀብት አስባሰብም ሆነ ሌሎች የንቅናቄ ሥራዎችን ወደ ላቀ ደረጃ እንዲያደርስ ተልዕኮ ተሰጥቶታል።

በአዲስ መልክ የተቋቋመው ምክር ቤት ዘጠኝ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አሉት መሆኑ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ ÷የምክር ቤቱ ሰብሳቢ፣የአዲስ አበባ ከተማ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘመን ጁነዲ ደግሞ ምክትል ሰብሳቢ ሆነዋል።

ኢንጂነር እንዳወቅ በዚሁ ወቅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እየተከላከሉ ለግድቡ ግንባታ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ማሳደግ አለብን ብለዋል።

ግድቡ የኢትዮጵያዉያን የታላቅነት መገለጫ በመሆኑ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።

የመንግሥትም ሆነ የምክር ቤቱ አመራር የግድቡን ግንባታ ጉዳይ ከመደበኛ ሥራው ጋር አስተሳስሮ ማከናወን ይገባዋል ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ናቸው።

ልዩነትን ወደ ጎን በመተው በአንድነት ሆነን ግድቡን ማጠናቀቅ አለብን ሲሉም አስገንዝበዋል።

የምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የግድቡ ባለቤት የሆነውን ሕዝብ ተሳትፎ ለማጎልበት እንደሚሰሩ በዚሁ ወቅት መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የግድቡ ግንባታ 73 ነጥብ 7 በመቶ መድረሱም ተገልጿል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.