Fana: At a Speed of Life!

“የአባይ ወንዝ ፖለቲካና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ” በሚል ርዕስ አገር አቀፍ አውደ-ጥናት በደብረ-ታቦር ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) “የአባይ ወንዝ ፖለቲካና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ” በሚል ርዕስ አገር አቀፍ አውደ-ጥናት በደብረ-ታቦር ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል።

የዩኒቨርስቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር መንበሩ ተሾመ ዩኒቨርስቲው ከዚህ ቀደምም ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምሮችን ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን፥ ይህ አውደ-ጥናትም ሀገራችን እያካሄደችው ላለው የአባይ ውሃ አጠቃቀም ድርድር አጋዥ ሃሳቦችን የሚያቀርብ ነውም ብለዋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድሩ የህግ አማካሪ አቶ መርሐ ፅድቅ መኮንን በበኩላቸው አለም አቀፉ የውሃ ስምምነት ኢትዮጵያም የአባይን ወንዝን በፍትሃዊነት የመጠቀም መብት እንዳላት የሚያመላክት ቢሆንም እስከ አሁን ግን ይህንን መብት ለመጠቀም አልተቻለም ነበር ብለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለሀገሪቱ ያለው ፋይዳ ከታወቀ በኋላና ስራው ከተጀመረ ወዲህ ግን በርካታ ድርድሮች እየተካሄዱ በመሆናቸው ይህንን መሰል አገር አቀፍ አውደ ጥናት አስፈላጊና መፍትሄ አመንጪ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

በውይይቱ የአባይ ወንዝንና የአጠቃቀም ሂደቶችን የተመለከቱ ጥናታዊ ፅሁፎች እየቀረቡ ይገኛሉ።

በሙሉጌታ ደሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.