Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ሃገራት አዲስ የእንቅስቃሴ ገደቦችን እየጣሉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሃገራት አዲስ የእንቅስቃሴ ገደቦችን እየጣሉ ነው።

በብሪታንያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊየን መሻገሩን ተከትሎ ለአንድ ወር የሚቆይ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አዲሱ የእንቅስቃሴ ገደብ እስከ ፈረንጆቹ ታህሳስ 2 ቀን እንደሚቆይ ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎም ዜጎች ለትምህርት፣ ስራ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግና አስፈላጊ ለሆኑ ጉዳዮች ብቻ ከቤት መውጣት ይፈቀድላቸዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም አስፈላጊና ወሳኝ የተባሉ የትምህርትና የጤና ተቋማት ሳይዘጉ ይቆያሉ ተብሏል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ ሌሎች ታላላቅ ስፖርታዊ ውድድሮችም ባሉበት ይቀጥላሉ ነው የተባለው።

ከዚህ ባለፈም ኦስትሪያ ከምሽት እስከ ንጋት የሚቆይ የሰአት እላፊ ገደብ ጥላለች።

የካፌና የምግብ ቤት አገልግሎትም ዳግም ዝግ እንዲደረግ የሃገሪቱ መንግስት ወስኗል።

እንዲሁም ግሪክ በከፊል እና ፖርቹጋል ደግሞ በአብዛኛው የሃገሪቱ አካባቢ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥለዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ እና ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.