Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረትና የጀርመን መንግሥት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 22 መኪኖችን አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአውሮፓ ህብረትና የጀርመን መንግሥት በጋራ ያበረከቱለትን 22 መኪኖች ተረክቧል፡፡
የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በተገኙበት የተፈጸመው ርክክብ 12 ሃርድ ቶፕ እና 10 ፒክ አፕ መኪኖችን ያካተተ ነው።
ዋና ሰብሳቢዋ ቦርዱ የሎጅስቲክ እንቅስቃሴ ላይ ያለበትን ውስንነት በመግለፅ እንዲሁም ቦርዱ በመንግሥትም ሆነ በአውሮፓ ሕብረት የሚደረጉለት ድጋፎች አስፈላጊነት ገልጸው ምስጋና ማቅረባቸውን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.