Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ታዛቢዎችን እንደሚልክ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ በቀጣይ ለምታካሂደው ሀገራዊ ምርጫ ታዛቢዎችን እንደሚልክ ገለፀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይና የፀጥታ ፖሊሲ ኃላፊ እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦሬል ፎንተልስ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦሬል ጋር ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና የምታደርገውን ጉዞ እንዲሁም የቀጠናውን ጉዳዮች በተመለከተ ተወያይተናል ብለዋል።

በውይይቱ ወቅትም ኢትዮጵያ በለውጥ ጎዳና የምታደርገውን ጉዞ በቆራጥነት እንደምትቀጥል እንደገለጹላቸውም በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይና የፀጥታ ፖሊሲ ኃላፊ እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦሬል፥ ህብረቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ላለው የለውጥ ስራ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ቀጣዩን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ለመታዘብ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላክም ገልፀዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.