Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ለአፍሪካ ቀንድ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ድጋፍ ወደ 430 ሚሊየን ዩሮ ከፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 24፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የአውሮፓ ህብረት ለአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚያደርገውን አስተዋፅኦ እንደሚያጠናክር በህብረቱ የአለም አቀፍ ግንኙነት ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽነሯ በ13ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢንሼቲቭ  የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ህብረትን በመወከል ተሳትፈዋል፡፡

በስብሰባው ወቅት ኮሚሽነሯ የአውሮፓ ህብረት ለአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ቀደም ሲል ካደረገው የ162 ሚለየን ዩሮ ድጋፍ በ2022 ወደ 430 ሚሊየን ዩሮ ከፍ በማድረግ ለምግብ ዋስትና የሚያደርገውን አስተዋፅኦ እንደሚያጠናክር ገልፀዋል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት የሶማሊያን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማስቀጠል የ13 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ የበጀት ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለፁት ጁታ ኡርፒላይነን በተጨማሪም ለግንባታ፣ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚያስችል የ125 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ  እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት በተጨማሪም መሠረታዊ የትምህርትና የጤና ፍላጎቶችን ለመደገፍ 81 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ለመስጠት ማቀዱንም ኮሚሽነሯ ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽነሯ ኡርፒላይነን የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በኮቪድ 19፣ በድርቅ እና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ክፉኛ የተጎዳ ክልል መሆኑን ጠቅሰው በዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ምክንያትም በቀጠናው የምግብ ቀውስ እየተከሰተ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.