Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት በሊቢያ ከጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘ በሶስት ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጣለ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 11 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት በሊቢያ ከጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘ በሶስት ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ መጣሉን አስታውቋል ።
 
የአውሮፓ ህብረት በሶስት ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ የጣለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሊቢያ ላይ ከጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘ የጣለውን ማዕቀብ ጥሰዋል በሚል ነው።
 
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት÷ ሩሲያ ፣ ቱርክ ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ሌሎች መንግስታት በሊቢያ ላይ የሚደረገውን አለም አቀፍ የጦር መሳሪያ እቀባን በግልጽ ጥሰዋል ሲል ከሷቸዋል።
 
በብራሰልስ የተካሄደው የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በሶስቱ ኩባንያዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ የንብረት እቀባን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
 
ኩባንያዎቹ የቱርክ፣ የካዛኪስታንና የጆርዳን መሆናቸውም ነው የተነገረው።
 
ከዚያም ባለፈ ህብረቱ በሁለት ግለሰቦች ላይ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ማዕቀበ መጣሉን አስታውቋል ።
 
ይህ የህብረቱ ማዕቀብ በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ለውጦች ምላሽ ለመስጠትና ያለውን የፖለቲካ ሂደት በመደገፍ ያለፈ እና ሊከሰቱ የሚችሉ የህግ ጥሰቶች እና አመጾችን ለመከላከል ያለመ መሆኑንም ነው በመግለጫው የተገለጸው።
 
በሊቢያ ለረጅም ጊዜ በስልጣን የነበሩት ሙአመር ጋዳፊ በአውሮፓውያኑ 2011 በኔቶ ድጋፍ በሚያገኙ ኃይሎች ከስልጣን ተወግደው ከተገደሉ ወዲህ ሊቢያ ግጭት ውስጥ መሆኗ ይታወቃል።
 
ምንጭ፡-ቢቢሲ
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.