Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ለሰብአዊ ድጋፍ ከ53 ሚሊየን ዩሮ በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት በትግራይና ሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች የሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች 53 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖችን ጨምሮ በግጭትና በአየር ንብረት ለተጎዱ ወገኖች የሚውል እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

የህብረቱ የቀውስ አመራር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺቺ ድጋፉ ትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሰብአዊ ድጋፍ ማድረስ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በተለያየ መልኩ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳትና በሚገኙበት አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማገዝ ይውላልም ተብሏል፡፡

ኮሚሽነሩ በነገው ዕለት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር እንደሚወያዩ ከህብረቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.