Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሦስት ሃገራት የ23 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሦስት ሃገራት የ23 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ድጋፉ ሱዳን እና ኬንያን እንደሚያካትት ህብረቱ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

ከ23 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ውስጥ 18 ነጥብ 8 ሚሊየን ዩሮው በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚውል መሆኑን ነው የጠቀሰው፡፡

እንዲሁም ሁለት ሚሊየን ዩሮው ደግሞ ለሱዳን የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ዮሮ የሚሆነው ደግሞ በኬንያ የምግብ ዋስትና ለተጋረጠው አደጋ የሚውል መሆኑ ነው የገለጸው፡፡

የአውሮፓ ህብረት በፈረንጆቹ 2020 ለኢትዮጵያ ያደረገው ድጋፍ 63 ነጥብ 2 ሚሊየን ዩሮ መድረሱን ገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.