Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ የሚያገኘውን ጋዝ ለመተካት ቢያንስ ሶስት አመታት ያስፈልገዋል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ የሚያገኘውን ጋዝ ለመተካት ቢያንስ ሶስት አመታት ያስፈልገዋል ሲል ዓለም አቀፉ ደረጃ አውጪ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
ሞስኮ አቅርቦቷን ካቋረጠች ስሎቫኪያ፣ ሃንጋሪ እና ቼክ ሪፐብሊክ በጋዝ እጦት ሳቢያ በጣም ይጎዳሉ ሲል ኤጀንሲው ገልጿል።
የጋዝ አቅርቦቱ በድንገት መቋረጥ የኤጀንሲው መሰረታዊ ጉዳይ አይደለም ሲልም አስገንዝቧል።
አሁን ላይ ቡልጋሪያ እና ፖላንድ የጋዝ አቅርቦቱ የተቋረጠባቸው ሲሆን፥ የሌሎች የህብረቱ አባል ሀገራት አቅርቦት መቀነሱንም ኤጀንሲው አስታውቋል።
የጋዝ አቅርቦቱ መቋረጥ ከሚያስከትለው ማህበራዊ ጫና ባለፈ፥ በሀገራቱ ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና እና ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያስከትላልም ብሏል።
ባለፈው ሚያዝያ ወር ሩሲያ ጋዝ መግዛት የሚፈልጉ ሀገራት በሩሲያ መገበያያ ገንዘብ ክፍያ እንዲፈጽሙ መጠየቋ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎ ሀገራት ይህን የሩሲያ ትዕዛዝ አንፈጽምም በማለታቸው ሩሲያ የጋዝ አቅርቦቷን ማቋረጧና ለተወሰኑ ሀገራትም መቀነሷ ይታወሳል።
በያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢም ለጀርመን የምታቀርበውን የጋዝ ምርት “በቴክኒካዊ ችግር ምክንያት” በሚል በ60 በመቶ መቀነሷን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.