Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዘመቻ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በወረርሽኙ ከተጠቁት አህጉራት መካከል አንዱ የሆነው የአውሮፓ ህብረት የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚረዳውን የክትባት ዘመቻ በይፋ ጀምሯል፡፡

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሊየን በትናትናው ዕለት ለ27ቱ አባል ሃገራት የሚውል የፋይዘርና የባዮንቴክ ክትባት መሰራጨቱን ተናግረዋል፡፡

የጀርመን የጤና ሚኒስትር እና የጣልያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክትባቱ ወረርሽኙን ለመመከት የሚረዳ ቁልፍ ነገር መሆኑን ገልጸው ወደ ተለመደው ህይወት ለመመለስ የሚረዳ ነው ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡

አንዳንድ አባል ሃገራት ለወረርሽኙ ተጋላጭ ናቸው ያሏቸውን ዜጎች ከትናትናው ዕለት ጀምሮ መስጠት የጀመሩ ሲሆን አብዛኛዎች ሃገራት ደግሞ ዛሬ ጀምረዋል፡፡

ዘመቻው የተጀመረው ሁሉም የአውሮፓ አባል ሃገራት ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎችን ባስተላለፉበት ወቅት ላይ ነው ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በብሪታንያ የታየው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሸኝ ወደ ተለያዩ አባል ሃገራት መሰራጨቱም እየተነገረ ይገኛል፡፡

446 ሚሊየን ህዝብ በያዘው የአውሮፓ ህብረት እስካሁን ከ14 ሚሊየን ህዝብ በላይ በኮሮና ቫይረስ ሲያዝ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ 335 ሺህ ሰው ለህለፈት ተዷርጓል፡፡

ህብረቱ ከመድሓኒት አምራች ኩባንያዎች ጋር 2 ቢሊየን መጠን የያዘ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለማግኘት ከዚህ ቀደም ስምምነት ላይ መድረሱንም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.