Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት 20 በሚደርሱ የቤላሩስ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ሊጥል ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት 20 በሚደርሱ የቤላሩስ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ሊጥል ነው፡፡

የህብረቱ አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከፍተኛ ባለስልጣናቱን በጥቁር መዝገብ በማስፈር ማዕቀብ ለመጣል ተስማምተዋል፡፡

ማዕቀቡ በሃገሪቱ ከምርጫ ውጤት መጭበርበርና እሱን ተከትሎ ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰልፈኞች ላይ ተወስዷል ከተባለው የሃይል እርምጃ ጋር በተያያዘ የሚጣል መሆኑም ተገልጿል፡፡

የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮም በማዕቀቡ ዝርዝር ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ ነው የተባለው፡፡

ማዕቀቡን ለመጣል የሚያስችሉ ህጋዊ ሂደቶች ምናልባትም ሳምንት ሊቆይ ይችላልም ተብሏል፡፡

ማዕቀቡ የጉዞ ክልከላ እና የገንዘብና ንብረት ማገድን ጨምሮ የተለያዩ ክልከላዎችና ገደቦችን የሚያካትት ይሆናል፡፡

በቤላሩስ ከምርጫው ጋር ተያይዞ ከተፈጠረው ህዝባዊ ተቃውሞ በኋላ በርካታ ሃገራት ፊታቸውን እያዞሩ ነው፡፡

በአንጻሩ ሩሲያ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞች “ስርአት አልበኛ” እንዳይሆኑ በማስጠንቀቅ በመጠኑም ቢሆን አጋርነቷን እያሳየች ትገኛለች፡፡

ምንጭ፣ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.