Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ እና እስያ የኢኮኖሚ ኅብረት ኢትዮጵያ ዋና የንግድ አጋራችን ናት አለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓና የእስያ የኢኮኖሚ ኅብረት እና ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2022 ትብብራቸውን የበለጠ ማሳደግ በሚችሉበት ዕቅድ ላይ ተወያዩ፡፡

የአውሮፓ እና የእስያ የኢኮኖሚ ኮሚሽን ጥምረት የልማት መምሪያ ዳይሬክተር የሆኑት ጎሃር ባርሴግያን ÷ በሩሲያ ከኢትዮጵያ አምባሳደር ዓለማየሁ ተገኑ ጋር በኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት ባደረጉት ውይይት የኢኮኖሚ ትብብር የጊዜው ቁልፍ ርዕሰ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋና የንግድ አጋራችን ሆና የቆየች ታሪካዊ ግንኙነታችን የጠነከረ ሀገር ናት ነው ያሉት ጎሃር ባርሴግያን።

ከፈረንጆቹ ጥር እስከ ጥቅምት 2021 በኢትጵያና በአውሮፓ – እስያ አባል ሀገራት መካከል የተካሄደው የንግድ ልውውጥም ከፈረንጆቹ 2020 ጋር ሲነጻጸር በ 4 ነጥብ 7 በመቶ ጥማሬ አሳይቷል ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዓለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው ÷ በኢትጵያ የሚመረቱት እንደ አበባ፣ ጨርቃጨርቅ፣ ቡና ፣ እና የመሳሰሉት ምርቶች በአውሮፓና በእስያ ገበያ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸውና ተወዳዳሪ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የአውሮፓ እና እስያ የኢኮኖሚ ኅብረትና ኢትዮጵያ ÷ ባለሐብቱን እና የንግድ ዘርፍ ላይ የተሰማራውን ማኅበረሰብ በማወያየት በምጣኔ ሐብት ትብብሩ ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡ ይበልጥ መሥራት ይገባልም ሲሉ አስምረውበታል፡፡

ጎሃር ባርሴግያን ÷ የአውሮፓ – እስያ የኢኮኖሚ ኮሚሽን እና የአፍሪካ ኅብረት በቀጣይ በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው መስኮች ላይ መነሻ መርሀ ግብር ነድፈው ለመንቀሳቀስ ዝግጅት ላይ መሆናውንም ጠቁመዋል፡፡

ተወያዮቹ ትብብሩን በማሳደግ እንደ “ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ መድረክ”፣ “የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ” እና ሌሎች ዓለም አቀፋዊ የውይይት መድረኮችን ለመቀላቀል ፍላጎት ማሳየታቸውን ከሩሲያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.