Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ መርሃ ግብር አስጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ መርሃ ግብር አስጀምሯል፡፡

በቢሮው የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ÷እኛ ኢትዮጵያውያን እርሳ በርስ መረዳዳትና መደጋገፍ ባሕላችን በመሆኑ በዘርና በሃይማኖት ሳንከፋፈል ሕብረ ብሔራዊ ሀገር መገንባት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት በበኩላቸው÷ ኮርፖሬሽኑ በነባር ክፍለ ከተሞች የከፋ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች እስከ 150 ቤቶችን ለመጠገንና ለማደስ መታቀዱን ተናግረዋ፡፡

ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ቤታቸው የሚታደስላቸው ነዋሪዎች ያለባቸውን ችግር በመረዳት ቤቶቹ ፈጥነው ታድሰው ነዋሪዎቹ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ ለማድረግ መረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡

የአራዳ ክፍለ ከተማ በጎፍቃድ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንግስቱ ግዛቸው÷ ክፍለ ከተማው በዘንድሮ ዓመት የክረምት በጎ ፍቃድ መርሃ ግብር 198 ቤቶችን ለማደስ አቅዶ የ119 ቤቶች እድሳት ማስጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

በሃይማኖት እያሱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.