Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በኢ/ር ታከለ ኡማ የቀረበውን ሹመት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ኢንጅነር ታከለ ኡማ ለከተማዋ ምክር ቤት የተለያዩ የስራ ሃላፊነት ያቀረቡትን ሹመት አጸደቀ።

በመደበኛ ስብሰባው ከተገኙት 89 አባላት ውስጥ ሹመቱን በ79 ድጋፍ፣ በ3 ተቃውሞ እና በ7 ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

ተሿሚዎቹም በምክር ቤቱ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

በዚህ መሰረት፡-

1 . ኢንጅነር እንዳወቅ አብጤ – በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አስተባባሪ

2. ኢንጅነር ሰናይት ዳምጠው- የቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ

3. ወይዘሮ ነጂባ አክመል – የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ

4 አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ – የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ

5 አቶ አብዱልቃድር መሀመድ – ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ

6 ወይዘሮ ኤፍራህ አሊ- የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ

7 አቶ ሀይሉ ሉሌ – የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ

8 አቶ ዘላለም ሙለታ – የትምህርት ቢሮ ሃላፊ

9 ኢንጅነር ደመላሽ ከበደ- የኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ

10 አቶ ስጦታው ታከለ – የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ

11 አቶ ነጋሽ ባጫ- የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ ሃላፊ

12 አቶ ይመር ከበደ – የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ሃላፊ

13 አቶ መኮንን ተፈራ- የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ

14 አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ- የንግድ ቢሮ ሃላፊ

15 አቶ አዱኛ ደበላ- የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ

16 አቶ አብርሃም ታደሰ- የወጣቶች በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ

17 አቶ ዋቁማ አበበ – የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር

18 አቶ ታምራት ዲላ- የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር

19 አቶ ታዜር ገብረእግዚአብሄር – የኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሾመዋል።

በተስፋዬ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.