Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት ልዩ ልዩ ሹመቶችን አጸደቀ።

በዚህ መሠረት፦

1ኛ. አቶ ጥራቱ በየነ – በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ ኃላፊ

2ኛ. ዶክተር መስከረም ፈለቀ – ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

3ኛ . ኢንጂነር አያልነሽ ሀ/ማርያም – ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ

4ኛ. ዶክተር መስከረም ምትኩ – የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር

5ኛ. ዶክተር ሚልኬሳ  ጃጋማ – መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

6ኛ. ዶክተር ሙሉቀን ሀብቱ – ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

7ኛ. አቶ ተፈራ ሞላ – ሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮ ኃላፊ

8ኛ. አቶ ሙሉጌታ ተፈራ – ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤ ለከተማው ምክር ቤት ለሹመት ካቀረቧቸው የቢሮ ሃላፊዎች በተጨማሪ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የአመራር ሽግሽግ እና አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥተዋል።
 
ሹመቶቹም የትምህርት ዝግጅትን፣ የስራ ልምድን እና የአመራር ብቃትን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን የተጀመረው ሪፎርም በተደራጀ አመራር አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሆነ ገልጸዋል።
 
በዚሁ መሰረት÷
 
1ኛ. ዶክተር እመቤት ጌታነህ – አራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
 
2ኛ. ወይዘሮ ነጻነት ዳባ – ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
 
3ኛ. አቶ ሙቀት ታረቀኝ – ኮልፌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
 
4ኛ. ወይዘሮ ሽታዬ መሀመድ – ልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
 
5ኛ. ወይዘሮ ፈቲያ መሀመድ – አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
 
6ኛ. አቶ አባዌ ዮሀንስ – ጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
 
7ኛ. አቶ አስፋው ተክሌ – የካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
 
8ኛ. አቶ ኤልያስ መሀመድ – ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
 
9ኛ. አቶ ጀማል ረዲ – ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
 
10ኛ. አቶ መኮንን አምባዬ – ቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
 
11ኛ. አቶ ይታያል ደጀኔ – አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን ተሹመዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.