Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር መቀሌ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መቀሌ ገብተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦሪዲን በድሪን የያዘው ልኡክ ወደ መቀሌ ያቀናው በህግ ማስከበሩ ሂደት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መሆኑም ነው ተገለጸው፡፡

ልኡካኑ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና የካቢኔያቸው አባላት፣ የመቀሌ ከተማ የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የኃይማኖት አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በሁለቱም የመንግስት አመራሮች የሚመራው ልኡክ በቆይታው ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ይወያያል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.