Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቤኒሻንጉል  ጉምዝ ክልል 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የከተማ አስተዳደር የከንቲባ የህዝብ አደረጃጀት አማካሪ አቶ ሺሠማ ገብረ ስላሴ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አስረክበዋል።

በድጋፍ ርክክቡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ታረቀኝ ቴሲሳ እንደገለፁት የከተማ አስተዳደሩ ላደረገው የምግብ እህል የሰብዓዊ ድጋፍ  ምስጋና አቅርበዋል።

ከከተማ አስተዳደሩ የተበረከተው ድጋፍ በክልሉ በችግር ውስጥ ለሚገኙ  ዜጎች ምላሽ ለመጠት እየተሰራ ላለው ስራ አጋዥ እንደሚሆን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

አቶ ሺሠማ ገብረ ስላሴ በበኩላቸው በመተከል ዞን በንፁኃን ዜጎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት ሁሉንም ያሳዘነ ድርጊት በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ በጽኑ እንደሚያወግዘው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያን አንድነት የማይፈልጉ አካላት ሴራ ይበልጥ አንድነታችንን ያጠናክሩታል ያሉት አቶ ሺሰማ በክልሉ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሆን 8 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት እያንዳንዳቸው 1 ሺህ ኩንታል የያዙ የስንዴ፣ የጤፍ እና የበቆሎ ድጋፍ ተደርጓል ማለታቸውን ከአዲስ አባባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም የህግ የማስከበር የህልውና ዘመቻ አስተዋጽዕዎ ላበረከቱ የአማራ እና የአፋር የፀጥታ ሀይሎች እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎችን ለመደጎም  ቃል በገባው መሠረት ለእያንዳንዳቸው 3 ሺህ ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.