Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕንጻዎችን ቀለም በተመለከተ ማብራሪያ ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕንጻዎችን ቀለም በተመለከተ ማብራሪያ ሰጠ።
አስተዳደሩ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እንድትሆን እና ዓለም አቀፍ ደረጃን የሚመጥን ገፅታ እንዲኖራት ከሚሠሩ ሥራዎች አንዱ የሕንጻዎችን ቀለምና ቁመት የሚወስን አሠራርን መተግባር መሆኑን አስታውቋል።
በእስካሁኑ ሂደት የከተማዋ ሕንጻዎች ያለምንም ቁጥጥርና ወጥነት በጎደለው መንገድ የሚቀቡ ቀለማት የከተማዋን መልክ ቡራቡሬና ዥንጉርጉር ከማድረጋቸውም በላይ÷ የሚገነቡ ሕንጻዎች ዲዛይን በዘፈቀደ መሠራቱ የከተማዋን ገፅታ በእጅጉ ጎድቶታልም ነው ያለው አስተዳደሩ፡፡
ስለሆነም ይህን ችግር መልክ ለማስያዝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከብዙ ዓለም አቀፍና አፍሪካዊ ከተሞች ተሞክሮ በመውሰድ÷ ለከተማዋ የሚስማማ የሕንጻ ቀለማት ደረጃን አጥንቶ ለውይይት አቅርቧል፡፡
በመሆኑም በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች በተሳተፉበት ሁኔታ ዝርዝር ጥናት በማድረግ ለከተማዋ የሚስማሙ 13 ዓይነት ቀለማት መለየታቸውን ገልጿል።
በዚህ መሰረት በሌሎች ሀገራት እንደሚደረገው ለከተማዋ በመለያነት ከተመረጡ ቀለማት መካከል የሕንጻ ባለንብረቶች የሚመርጡትን ወስደው የመጠቀም መብት ያላቸው ሲሆን÷ ይህ አሠራር በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች ተጀምሮ ወደ ትግበራ መገባቱንም ነው ያስታወቀው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.