Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ ተወስኖ የነበረው የመሬት ነክ አገልግሎት እግድ ተነሳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ አስተዳደር በጊዜያዊነት ታግዶ የነበረው የመሬት ነክ አገልግሎት እግድ መነሳቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
 
ጊዜያዊ እግዱ የተነሳ በመሆኑ አገልግሎቱን ከጥር 13 / 2014 ጀምሮ በየክፍለ ከተማው መስተናገድ እንደተጀመረ ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ከነሐሴ 7 ቀን 2013 ጀምሮ በጊዜያዊነት ታግደው የነበሩና እግዱ ከተነሳላቸው አገልግሎቶች መካከል ÷ ህጋዊ ሰነድ ላላቸው ይዞታዎች ብቻ ዋስትና እዳ መመዝገብ፣ የፍርድ ቤት እና የባንክ እግድ የመመዝገብና የመሰረዝ አገልግሎት (የእዳና እገዳ የማጣራት አገልግሎት)፣ የስመ ንብረት ዝውውር ስራ(በባንክ ሐራጅ የተሸጠ፣ በፍ/ቤት አፈፃፀም የተሸጠ፣ የኮንዶሚኒየም ቤት የስም ዝውውር አገልግሎት፥ እንዲሁም በውርስ የተላለፈ ንብረት እና በሪል እስቴትስ አልሚ የተፈፀመ የቤት ሽያጭ ይጠቀሳሉ፡፡
 
በተጨማሪም ለነባር ይዞታዎች የቦታ ኪራይና የቤት ግብር ተመን፣ የንብረት ግመታ፣ በይዞታ ይገባኛል ክርክር ፣ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማስረጃ መስጠት፣ የወሰን ይመላከትልኝ /የወሰን ችካል/፣ በከተማ አስተዳደር የሚታወቅ እና ቅድሚያ የሚሰጥ የልማት ተነሺ አገልግሎት (ካሣ ክፍያ፣ ምትክ ቤት እና ምትክ ቦታ አሰጣጥ አገልግሎቶች) ጊዜያዊ እግድ ከተነሳላቸው አገልግሎቶችም እግዱ የተነሳላቸው አገልግሎቶች ናቸው፡፡
 
እንዲሁም የቦታ ዝግጅት፣ የወሰን ማስከበር ተግባራት፣ በሊዝ በተላለፈ ቦታ ላይ የግንባታ ክትትል፣ የለማ መሬት በምደባ ወይም በጨረታ ማስተላለፍ፣ አዲስ ካርታ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች (የምትክ ኮንዶሚኒየም ቤት ለተወሰነላቸው፣ ለአመራር የሚሰጡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች እና የሪል እስቴትስ ተጠቃሚዎች /ቤት ገዥዎች የተናጠል ካርታ/መሆናቸውን አገልግሎቶች ጊዜያዊ እግዱ ተነስቶላቸዋል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.