Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 193 ምልምል ፖሊሶች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኮልፌ ኮንቲንጀንት የፖሊስ ማሰልጠኛ ማእከል ሲያሰለጥናቸው የቆያቸውን የ25ኛ ዙር 1 ሺህ 193 አዳዲስ ምልምል ፖሊሶችበዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ ፖሊስነት አገልግሎቱ ራስን ለሌሎች አሳልፎ እስከመስጠት ድረስ በምንም ነገር የማይተመን ትልቅ ስጦታ ነው፤ ፖሊስነት የከበረ ሙያ ነው ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ የሃገሪቱ ዋና ከተማና የዓለም አቀፍና የዲፕሎማቲክ መቀመጫ ናት ያሉት ከንቲባ  አዳነች÷ ከተማዋ እያደገችና ህዝብ ቁጥሯም እየሰፋ የሄደ በመሆኑ ብቃት ያለው እየተወሳሰበ የመጣውን ወንጀል ድርጊት መመከት የሚችል የፖሊስ ተቋም መገንባት ትኩረት የሰጠነው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

ተመራቂዎች በከተማዋ የሚታየውን ስርዓት አልበኝነት ማስቆምና የህግ የበላይነትም ማስከበር፤ ከህዝብ ጋር መተባበርና ማገልገል፤ፍትሃዊ መሆን ፤ከአድልዎ የነፃ አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡

እጅ ለእጅ ተያይዘን የከተማችንን ሰላም፤ የህዝባችንን ደህንነት ማስቀጠል ይኖርብናል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፡፡

ህዝባችን ከወንጀል ስጋት ነፃ መሆን አለበት፤ ማገልገል ክብር ነው፣ የራስን ህዝብና አገር ማገልገል ደግሞ ከክብር ሁሉ የላቀ ክብር ነው ማለታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.