Fana: At a Speed of Life!

የአዲግራት የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች በመቐለ ዩኒቨርስቲ ይመረቃሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በመቐለ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 30 እና ጥር 1 ቀን ሪፖርት አድርገው ትምህርት እንዲጀምሩ ተወስኗል፡፡

የህክምና ተማሪዎቹ ደግሞ በመቐለ ዩኒቨርስቲ አይደር ካምፓስ እንደሚገቡም ነው የተገለጸው፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ሳሙዔል በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ትምህርታቸውን በመቐለ ዩኒቨርስቲ እንዲያጠናቅቁ የተወሰነው የአዲግራት ዩኒቨርስቲ የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የጽህፈት ቤት ኃላፊው ውሳኔው የተላለፈው በአዲግራት ዩኒቨርስቲ የወርክሾፕ፣ የቤተሙከራ ቁሳቁሶችና የኔትወርክ ጥገና እስከሚጠናቀቅ ድረስ ነው ብለዋል፡፡

የጽህፈት ቤት ኃላፊው ወደ ሁለቱም የመቐለ ካምፓስ የተመደቡት የአዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጥር 2 ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ ነው የጠቀሱት፡፡

የመቐለ ዩኒቨርስቲ እና የራያ ዩኒቨርስቲ በቅርቡ ተመራቂ ተማሪዎቻቸውን ማስመረቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

ቀሪዎቹ በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችም ነባርና ተመራቂ ተማሪዎቻቸውን በቅርቡ ቅበላ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

በአወል አበራ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.