Fana: At a Speed of Life!

የአዳማ ከተማ አሰልጣኝ ራሳቸውን ከኃላፊነት ማንሳታቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዳማ ከተማ አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል ራሳቸውን ከኃላፊነት ማግለላቸውን አስታወቁ፡፡

አዳማ ከተማ ዛሬ ረፋድ ላይ በባህርዳር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና የ4 ለ  1 ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል የጨዋታውን መጠናቀቅ ተከትሎ በሰጡት አስተያየትም በገዛ ፍቃዳቸው ራሳቸውን ከኃላፊነት ማንሳታቸውን ተናግረዋል።

ከጨዋታው በፊትም ራሳቸውን ለማግለል ወስነው እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ከአመራሮች ጋር ተነጋግረው ዛሬ ለተካሄደው ጨዋታ መቅረባቸውን ከጨዋታው በፊት ለሱፐር ስፖርት የሰጡትን አስተያየት ጠቅሶ ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.