Fana: At a Speed of Life!

የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ዘርዓይ ሙሉን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አዲስ አሰልጣኝ መሾሙን አስታወቀ፡፡
አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል ራሳቸውን ከአዳማ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ማግለላቸው ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎም የአዳማ ከተማ ቦርድ አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡
አሰልጣኙ የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብን በሊጉ እንዲቆይ ማድረግ በዋናነት የተሰጣቸው የቤት ስራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
አዲሱ አሰልጣኝ ቡድኑን ጠንካራ ተፎካካሪ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው፥ አዳዲስ ለቡድኑ ይመጥናሉ የሚባሉ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ በማምጣት በክለቡ ብዙም ግልጋሎት ያልሰጡ ተጫዋቾችን ለመሸኘት በተጨማሪም አዲስ ረዳት አሰልጣኝ ወደ ክለቡ የማምጣት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
አሰልጣኝ ዘርዓይ የሀዋሳ ከተማን እና ሲዳማ ቡናን ከረዳት እስከ ዋና አሰልጣኝነት ማገልገላቸውን ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.