Fana: At a Speed of Life!

የአድዋ ድል በዓልን በአድዋ ከተማ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል በአድዋ ከተማ በማክበር የአይበገሬነት ተምሳሌት ለመሆን ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናቸውን በትግራይ ክልል የማዕከላዊ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የዞኑ አስተዳደር ከሚያስተዳድራቸው አንዷ በሆነችው አድዋ ከተማ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ነው አስተዳዳሪው ያስታወቁት፡፡

በክልሉ የማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኔ ገብረጻዲቅ በሰጡት አስተያየት በትግራይ ክልል ከተካሄደው የህግ ማስከበር ጋር ተያይዞ ህዝቡ አስቸጋሪ ጊዜዎችን አሳልፏል፡፡

ሆኖም በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያዊያን ኩራት የሆነውን የአድዋ ድል በዓል በአድዋ ከተማ ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአድዋ አካባቢ ያለው የሰላም ሁኔታ አስቸጋሪ ነው በሚል ህብረተሰቡ መስጋት እንደሌለበትም ጠቁመዋል፡፡

የትግራይ ህዝብ ከህግ ማስከበሩ ጋር ተያይዞ በችግር ውስጥ ቢሆንም ይህን በዓል በደመቀ ሁኔታ ያከብራል ብለዋል፡፡

በዓሉ ያለ አንዳች የጸጥታ ስጋት እንዲከበርም ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም ተባብሮ መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የዞኑ አስተዳደርም በአድዋ ከተማ በዓሉን ለማክበር ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን እንደጠቆሙ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአድዋ ድል በዓል በሁሉም የኢትዮጵያ አካካቢዎች እየተከበረ መሆኑ ይታወቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.