Fana: At a Speed of Life!

የአድዋ ድል ክብረ በዓል ብቻ ሳይሆን የአሸናፊነት እና የተነሳሽነት ምንጫችን ነው – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአድዋ ድል ክብረ በዓል ብቻ ሳይሆን የአሸናፊነት እና የተነሳሽነት ምንጫችን ነው ሲሉ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

ሚኒስትሯ ይህን ያሉት 125ኛውን የአድዋ ድል በዓልን በተመለከተ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እና ዲፕሎማቶች በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ነው።

”አድዋ ለለውጣችን የጋራ ድላችን” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የውይይት መድረክ  ላይ አምባሳደሮች ፣ ዲፕሎማቶች እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች እየተሳተፍ ይገኛሉ።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከ125 አመት በፊት በዚች ሀገር ቅኝ ገዥ ተስፋፊዎች እና ወራሪዎች ድል የተመቱበት ቀን ሆኖ ተመዝግቧል ብለዋል።

ለጥቁሮች ነፃነት ፈር ቀዳጅ የሆነው የአድዋ ድል ክብረ በዓል በቻ ሳይሆን የአንድነታችን እና የአሸናፊነታችን ምንጭ ነውም ሲሉ ገልጸዋል።

አባቶች የአድዋ ድልን ለማስመዝገብ ረጅም ረቀት እንደተጓዙ ሁሉ እኛም ካለንበት ዘርፈ ብዙ ችግር ለመውጣት ጊዜ ያስፈልጋል ለዚህ ደግሞ ሁሉም የጋራ ርብርብ ሊያደርግ ይገባልም ነው ያሉት ።

በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ኩዌሲ ኳርቲ÷ የአድዋ ድል ለመላው ጥቁር ህዝብ የነፃነት ተምሳሌት ነው፤ ድሉ ለአፍሪካውያን ብሎም ለመላው ዓለም ሊዳረስ ይገባልም ነው ያሉት።

አሁንም ጠንካራ አፍሪካን ለመመስረት ጠንካራ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ትስስር ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.