Fana: At a Speed of Life!

የአጋሮ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ በሶስት ወራት እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀመጠ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከሶስት ዓመት በፊት ግንባታው የተጀመረው የአጋሮ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ እንዲጠናቀቅ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጫልቱ ሳኒ አቅጣጫ አስቀመጡ።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ በጂማ ዞን አጋሮ ከተማ ጉብኝት አድርገዋል።
የአጋሮ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ 10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውቅ ሲሆን በ440 ሚሊየን ብር ነው እየተገነባ የሚገኘው።
በስራው ላይ ያለው ሆማ ኮንስትራክሽን በወሰን ማስከበር ችግር እና የግንባታ ቁሳቁሶች እጥረት ምክንያት ችግሮቹ መፈጠራቸውን ገልጿል ።
የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ ከ1 ሺህ 600 በላይ ቤቶች ለፕሮጀክቱ ሲባል ብቻ ማስነሳቱን ተናግሯል።
ወይዘሮ ጫልቱ ÷ ግንባታውን እያካሄደ ያለው ድርጅት መሠል ችግሮችን እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ የዚህ መንገድ ግንባታ በሶስት ወር ውስጥ አስፓልት እንዲለብስ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በሌላ በኩል ርዕሰ መስተዳድሯ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች በመልካምነት የሚነሱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በአፈወርቅ አለሙ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.