Fana: At a Speed of Life!

የአጣዬ ከተማን የመብራት አገልግሎትን ድጋሚ ለማስጀመር የኬብል እና የመንገድ ላይ መብራት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአጣዬ ከተማን የመብራት አገልግሎትን ድጋሚ ለማስጀመር የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የኬብል እና የመንገድ ላይ መብራት ድጋፍ በማሰባሰብ ለከተማ አስተዳደሩ ማስረከባቸውን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሃመድ ተናገሩ፡፡
 
ሚኒስትር ዴኤታው የመንገድ ላይ መብራቶቹ የከተማው ነዋሪዎች በፈለጋቸው ሰዓት እንዲንቀስቀሱና ደህንነት እንዲሰማቸው ለማድረግ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
 
የአጣዬ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የኤፍራታና ግድም ወረዳ አስተዳደር አመራሮች ከተማዋንና አከባቢውን መልሶ ለመገንባትና የህዝቡን የመሰረተ ልማት ፍላጎት ለማሟላት የምታደርጉት ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡
 
በቀጣይም በተቻለው አቅም ሁሉ የከተማዋንና አከባቢውን ነዋሪዎች ችግር ለመፍታት በጋራ እንሰራለን ነው ያሉት፡፡
 
የከተማዋና አከባቢው ነዋሪዎችም ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው እየተመለሱ መሆኑን በመመልከታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
 
የአካባቢው ተወላጆች በሙያቸው የሚያደርጉት እገዛ እጅግ የሚመሰገን መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው÷ለአብነትም የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሀዋሳ ዲስትሪክት ኢንፎርስመንት ቢሮ ስራ አስኪያጅ አቶ አስጨናቂ ካሳየ የአንድ ወር ፍቃድ በመውሰድ የከተማዋን የመብራት ዝርጋታ ሲሰሩ መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡
 
በተለያየ ቦታና የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ የአካባቢው ተወላጆችና ወዳጆች በሙያቸው የሚችሉትን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
ሁሉም ሲተባበር የሚታይ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ባለፉት ወራት በአጣዬ ከተማ የተሰራው ስራ ማሳያ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
 
ሚኒስትር ዴኤታው ጉዳዩን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ ድጋፉን ላደረጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በከተማዋ ነዋሪዎች ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.