Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሃገራት የኮቪድ-19 ክትባት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሃገራት የኮቪድ-19 ክትባት መስጠት መጀመራቸው ተነገረ፡፡

ግብጽ እና ጋና የኮቪድ- 19 ክትባት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፤ ናይጄሪያን ጨምሮ ሌሎች ሃገራትም ክትባቱን ዛሬ ይጀምራሉ ተብሏል፡፡

እስካሁን በአህጉሪቱ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ3 ሚሊየን 937 ሺህ በላይ ሲሆን፣ በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ104 ሺህ 900 በላይ ሆኗል፡፡

ቫይረሱ በፍጥነት እየተሰራጨ መምጣቱን ተከትሎ ውጤታማ የሆኑ ክትባቶች ለሃገራት እየተላኩ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

እድሜያቸው የገፋ እና የህክምና ባለሙያዎች ክትባቱን በቅድሚያ ይወስዳሉ፡፡

እስካሁን ዓለም ላይ ከ116 ሚሊየን 250 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን እና ዎርልድ ኦ ሜትር

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.