Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪማሃማት ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በተደረገላቸው ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸውን አስታወቁ።

ሙሳ ፋኪ ማሃማት ከእሳቸው የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው የሥራ አጋሮች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ በትናንትናው ዕለት እራሳቸውን ወደ ለይቶ ማቆያ እንዳስገቡ መናገራቸው ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ  ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው መረጋገጡን  በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

የህክምና ባለሙያዎች በሰጧቸው ምክር መሰረትም ለሚቀጥሉት 14 ቀናት ራሳቸውን ከሌሎች ለይተው እንደሚቆዩ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.