Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሕብረት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚደረግላቸው ሰዎችን 10 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ ሕብረት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚደረግላቸው ሰዎችን 10 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱ ተነግሯል፡፡

ሕብረቱ በኮሮና ቫይረስ የሚመረመሩ ሰዎችን ቁጥር በመላ አህጉሪቱ ቁጥሩን ለመጨመር ዕቅድ መያዙ ነው የተነገረው፡፡

በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት ወራት የሚመረመሩ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ሚሊዮን ከፍ የማድረግ አላማ እንዳለው ተሰምቷል ።

ሆኖም ባለሙያዎች በአፍሪካ ያለውን ዝቅተኛ ቁጥርተከትሎ በርካታ ሰዎችን ቫይረሱ እያለባቸው ሳይመረመሩ እንዳይቀሩ ስጋት እንዳለ ተነግሯል።

የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከል እስካሁን ድረስ 2ነጥብ4 ሚሊዮን ምርመራዎች መካሄዳቸውን ጠቅሷል።

በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሩን በሶስት እጥፍ ለማሳደግ እቅድ ያለ ሲሆን በዚህም ከአጠቃላይ የአፍሪካ ሕዝብ አንድ በመቶ ያህሉ ይመረመራሉ ተብሏል።

ይህም የአፍሪካ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት አጠቃላይ ሁናቴ እንደሚያሳይ ነው የተገለጸው።

በዚህም የአፍሪካ ሕብረት ለሁሉም አገራት እኩል የመመርመሪያ መሳሪያ ለመስጠት ማቀዱነው የተነገረው።

የአፍሪካ ህብረት 100 ሺህ የጤና ባለሙያዎች ማሰልጠን እንዲሁም የሚሊዮኖችን ንክኪ መለየት እንዲችሉ ወደ ህብረተሰቡ ለማሰማራት አቅዷል።

በአህጉሪቱ እስካሁን 160 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የ4ሺህ 600 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.