Fana: At a Speed of Life!

የካፍ ፕሬዚዳንት የአፍሪካ ሱፐር ሊግ ውድድርን ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ከፊፋው አቻቸው ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ጋር በመሆን የአፍሪካ ሱፐር ሊግ ውድድርን በዛሬው እለት ይፋ አድርገዋል፡፡

ውድድሩ ይፋ በሆነበት ወቅት የታንዛኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቃሲም ማጃሊዋ ተገኝተዋል፡፡

ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ 24 ቡድኖችን የሚያሳትፈው የአፍሪካ ሱፐር ሊግ ውድድር በፈረንጆቹ ነሐሴ ወር 2023 እንደሚጀምር ተመላክቷል።

የሱፐር ሊግ አሸናፊው ቡድን የ11 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ሽልማት የሚበረከትለት መሆኑን ከካፍ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.