Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሴቶች መብት ፕሮቶኮል በመላው አፍሪካ ሊተገበር ይገባል – ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሴቶች መብት ፕሮቶኮል በመላው አፍሪካውያን ሴቶች ሊተገበር ይገባል ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ በአፍሪካ የሴቶች መብት ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራው የማፑቶ ፕሮቶኮል ዛሬ 19ኛ ዓመቱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ የማፑቶ ፕሮቶኮል ትግበራ በየጊዜው እየተሻሻለ ቢሆንም አንዳንድ ሀገሮች ግን እንዳላጸደቁት አስታውቀዋል፡፡

አክለውም የአፍሪካ ሴቶች መብት ፕሮቶኮል በመላው አፍሪካውያን ሴቶች ሊተገበር እንደሚገባም ነው በመልዕክታቸው የተናገሩት፡፡

የማፑቶ ፕሮቶል የአፍሪካን ሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማረጋገጥን አላማው ያደረገ ስምምነት ነው።

ስምምነቱ የአፍሪካውያን ሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ማጠናከርና የውሳኔ ሰጪነት አቅማቸውን ለማሳደግ ያለመና በፈረንጆቹ 2003 የተደረሰ ስምምነት ነው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.