Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ወጣቶች የአህጉሪቱን ችግሮች በመጋፈጥ መፍትሄያቸው ላይ ሊያተኩሩ ይገባል- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ወጣቶች የአህጉሪቱን ችግሮች በመጋፈጥ መፍትሄዎቻቸው ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

የ2022 የፓን አፍሪካ ወጣቶች ስብሰባ በአዲስ አበባ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል፡፡

አቶ ደመቀ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር ÷ዛሬ በፓን አፍሪካን ስሜት መሰባሰብ ያለብን እንደቀድሞ አባቶቻችል ለነፃነት ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን አፍሪካ አሁንም ድህነት ውስጥ ናትና ከድህነት ለመውጣት በመሰባሰብ መስራት አለብን ብለዋል፡፡

ከምንም በላይ ደግሞ የአፍሪካ ወጣቶች ምቹ ሁኔታ የለም በማለት እና ችግሮችን በመፍራት ከመሰደድ ይልቅ ሁሉንም ነገር መጋፈጥ እና መታገል እንደሚገባቸው ነው የተናገሩት፡፡

በአፍሪካ ብዙ እውቀቶች አሉ፤ እነሱን በመጠቀም አፍሪካ እንድትበለጽግ እና እንድታድግ ወጣቶች የሚጠበቅባቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው÷ ወጣቶች የማህበራዊ ትስስት ገጾችን በአግባቡ በመጠቀም የአፍሪካን አንድነት ለማምጣት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በአፍሪካ ካለው ህዝብ ውስጥ 65 በመቶ የሚሆነው ወጣቱ መሆኑን አንስተውም÷ይህን በመጠቀም ብዙ ነገር መለወጥ እንችላለን ብለዋል፡፡

 

 

በ20 63 የበለጸገች አፍሪካን ለመፍጠር የተያዘውን እቅድ ለማሳካትም የአፍሪካ ወጣቶች ራዕዩን ከመደገፍ ባለፈ ትስስር አና አንድነት መፍጠር እንዳለባቸው ሚኒስትሯ ጠቁመዋል፡፡

በጥበበስላሴ ጀንበሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.