Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ በዓል በሆራ አርሰዴ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል ከንጋቱ ጀምሮ በሆራ አርሰዴ በተከናወነ ስነስርዓት ተከበረ።

የበዓሉ ስነ ስርዓት በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባገዳዎች ምርቃት ነው የተጀመረው፡፡

በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሆራ አርሰዴ በማቅናት በባህሉ መሰረት ለፈጣሪያቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የኢሬቻ በዓል የምስጋና፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ የእርቅና የይቅርታ በዓል ነው።

ኢሬቻ የምስጋናና የምልጃ በዓል ሲሆን በዚህ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ ሁሉን ነገር ለፈጠረው ምድርንና ሰማይን፣ ወንዝንና ባህርን፣ ቀንንና ሌሊትን፣ ብርሀንና ጨለማን፣ ሕይወትና ሞትን፣ ክረምትንና በጋን፣ ዝናብንና ሐሩርን፣ ዕጽዋትን፣ እንስሳትንና ሰውን ለፈጠረ፤ ሁሉን ነገር ማድረግ ለሚችል ዋቃ (አምላክ) ምስጋናና ክብር የሚያቀርብበት በዓል ነው።

የዘንድሮው በዓል በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በስፍራው በተመጠነ የሰው ብዛት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.